የ2018 የአዲስ ዓመት ዋዜማ ገበያ በምስል

በአዲስ ዓመት ዋዜማ ዶሮ ለመግዛት የሚከራከሩ ነጋዴ እና ገበያተኛ
የምስሉ መግለጫ, ኢትዮጵያውያን በእንቁጣጣሽ እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ ወይም በቅርጫም ቢሆን የበሬ ሥጋ በመጫረት በዓሉን ያደምቁታል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

አሮጌው ዓመት 2017 ተጠናቆ አዲሱን ዓመት ተቀብለናል።

የዛሬው መስከረም 01/2018 ዘመን መለወጫ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

ኢትዮጵያውያን በእንቁጣጣሽ እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ ወይም በቅርጫም ቢሆን የበሬ ሥጋቸውን በመጫረት ክብረ በዓሉን ያደምቁታል።

የሽንኩርቱ ቁሌት፣ የቅቤው ሽታ፣ የቡናው መዓዛና የእጣኑ ሽታ በየቤቱ ያውዳል።

የእርዱ ሁካታ፣ የዘመድ አዝማዱ ሳቅ፣ የአገር ባህል ልብሱ፣ ሙዚቃው የአውደ ዓመቱ መገለጫዎች ናቸው።

ቢቢሲ አማርኛ በበዓሉ ዋዜማ በአዲስ አበባ የተወሰኑ ስፍራዎች ተዘዋውሮ የገበያውን ሁኔታ በምስል አስቀርቷል።

የዶሮ ገበያ
የምስሉ መግለጫ, ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ዓውደ ዓመቶች ዶሮ በማረድ እና ከወዳጅ ዘመድ ጋር በጋራ ማዕድ በመቋደስ በዓሉን ያሳልፉታል
የአዲስ ዓመት ዋዜማ ቄጤማ ገበያ
የምስሉ መግለጫ, አዲስ ዓመትን ከሚያደምቁ መካከል አደይ አበባ እና ቄጤማ አንዱ ሲሆን በርካቶችም ቤታቸውን ቄጤማ በመጎዝጎዝ ያደምቁበታል
በአዲስ ዓመት ዋዜማ የበግ ገበያ ላይ ቀንዱ ላይ ምልክት የተደረገበት በግ
የምስሉ መግለጫ, በርካቶች በአዲስ ዓመት በቻሉት አቅም ዶሮ፣ በግ በመግዛት እና በማረድ አውደ ዓመቱን ያከብራሉ
አደይ አበባ
የምስሉ መግለጫ, በእንቁጣጣሽ ወቅት የሚታየው አደይ አበባ የአዲሱ ዓመት ድምቀት ነው
በአዲስ ዓመት ዋዜማ የችቦ እና የአደይ አበባ ገበያ
የምስሉ መግለጫ, በበዓሉ ዋዜማ ምሽት ቤተሰብ በጋራ ተሰብስቦ ችቦ በማብራት አዲሱን ዓመት ይቀበላል
ለአዲስ ዓመት ዶሮ የሚሸጥ ነጋዴ
አደይ አበባ
የአዲስ ዓመት ዋዜማ የቄጤማ እና የችቦ ገበያ
ለአዲስ ዓመት የገዛውን በግ ተሸክሞ የሚሄድ ሰው