ኮሮናቫይረስ፡ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስችሉ ቀላል ተግባራዊ ስልቶች

ታትሟል

እራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ከምንከላከልባቸው መንገዶች አንዱ ማኅበራዊ ርቃታችንን በመጠበቅ ነው።

አገራት እና ግለሰቦች ሰዎች ማኅበራዊ ርቀታቸውን መጠበቅ የሚያስችሏቸውን ተግባሯዊ ዘዴዎችን አምጥተዋል።

ይህ አሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ነው። ሰዎች እራሳቸውን ዘና ለማድረግ ወደ መናፈሻዎች ሲሄዱ መቀመጥ ሚችሉት በክቦቹ ውስጥ ነው።
የምስሉ መግለጫ, ይህ አሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ነው። ሰዎች እራሳቸውን ዘና ለማድረግ ወደ መናፈሻዎች ሲሄዱ መቀመጥ ሚችሉት በክቦቹ ውስጥ ነው።
በስሪ ላንካ ሰዎች በአሳንስር ውስጥ በዚህ መልኩ ርቃታቸውን በመጠበቅ እራሳቸውን ከቫይረሱ ይከላከላሉ።
የምስሉ መግለጫ, በስሪ ላንካ ሰዎች በአሳንስር (ሊፍት) ውስጥ በዚህ መልኩ ርቃታቸውን በመጠበቅ እራሳቸውን ከቫይረሱ ይከላከላሉ።
በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው ምግብ ቤት መመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ካርቶን ላይ የተሳሉ ስዕሎት ይቀመጣሉ። ተጠቃሚዎች መቀመጥ የሚችሉት በባዶ ወንበሮች ላይ ነው። የስዕሎቹ መኖር ምግብ ቤቱ በሰው የተሞላ አይነት ስሜት እንዲፈጥር ያደርጋል ተብሎለታል።
የምስሉ መግለጫ, ሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኝ ምግብ ቤት መመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ካርቶን ላይ የተሳሉ ስዕሎት ይቀመጣሉ። ተጠቃሚዎች መቀመጥ የሚችሉት በባዶ ወንበሮች ላይ ነው። የስዕሎቹ መኖር ምግብ ቤቱ በሰው የተሞላ አይነት ስሜት እንዲፈጥር ያደርጋል ተብሎለታል።
ሰዎች በታይላንድ ባንኮክ በሚገኘው ምግብ ቤት ውስጥ ምሳ እየተመገቡ ነው። በሰዎች መካከል የተወጠሩት ላስቲኮች ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸውን ዝቅ ያደርጋሉ።
የምስሉ መግለጫ, ሰዎች ታይላንድ ባንኮክ በሚገኝ በዚህ ምግብ ቤት ውስጥ ምሳ እየተመገቡ ነው። በሰዎች መካከል የተዘረጉት የላስቲክ መከለያዎች ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸውን ዝቅ ያደርጋሉ።
የአልባኒያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማህበራዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ የተቀመጠላቸውን አቅጣጫ በመከተል ወደ ህንጻ ሲገቡ።
የምስሉ መግለጫ, የአልባኒያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበራዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ የተቀመጠላቸውን አቅጣጫ በመከተል ወደ ህንጻ ሲገቡ።
ይህ ደግሞ ሂውስተን ቴክሳስ ነው። ይህ የሴቶች የውበት ሳሎን በዚህ መልኩ ደንበኞቹን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይጥራል።
የምስሉ መግለጫ, ይህ ደግሞ ሂውስተን ቴክሳስ ነው። ይህ የሴቶች የውበት ሳሎን በዚህ መልኩ ደንበኞቹን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይጥራል።
ይህ ምስል ብራሰልስ ቤልጄም የሚገኙ ተማሪዎች ርቀታቸውን በመጠበቅ ሲነጋገሩ ያሳያል።
የምስሉ መግለጫ, ይህ ምስል ብራሰልስ ቤልጄም የሚገኙ ተማሪዎች ርቀታቸውን በመጠበቅ ሲነጋገሩ ያሳያል።
በፈረንሳይ ሰዎች ባቡር ሲጠብቁ ርቀታቸውን ጠብቀው ነው።
የምስሉ መግለጫ, በፈረንሳይ ሰዎች ባቡር ሲጠብቁ ርቀታቸውን ጠብቀው ነው።
በሳን ፍራንሲስኮ ቤት አልባ ለሆኑ ዜጎች መንግሥት ያዘጋጀው ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ርቀትን በጠበቀ መልኩ የተቋቋመ ነው።
የምስሉ መግለጫ, የአሜሪካ መንግሥት በሳን ፍራንሲስኮ ቤት አልባ ለሆኑ ዜጎች ያዘጋጀው ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ርቀትን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጅቷል ነው።
በባንኮክ ታይላንድ የሚገኝ ምግብ ቤት፤ ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠበቁ ለማስገደድ 'ፓንዳ' አሻንጉሊት በየ ወንበሮቹ ላይ አስቀምጧል። ሰዎች አሻንጉሊቱን አንስተው መቀመጥ አይችሉም። በዚህም ማህበራዊ ርቀንት ማስጠበቅ ተችሏል።
የምስሉ መግለጫ, በባንኮክ ታይላንድ የሚገኝ ምግብ ቤት፤ ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠበቁ ለማስገደድ 'ፓንዳ' አሻንጉሊት በየወንበሮቹ ላይ አስቀምጧል። ሰዎች አሻንጉሊቱን አንስተው መቀመጥ አይችሉም። በዚህም ማኅበራዊ ርቀንት ማስጠበቅ ተችሏል።
በስፔን ማድሪድ ሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ምዕመናን ብቻ ወደ ቤተ-መቅደሱ እንዲገቡ ይፈቅዳል።
የምስሉ መግለጫ, በስፔን ማድሪድ ሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ምዕመናን ብቻ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይፈቅዳል።
በሚላን ጣሊያን በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ አስተናጋጁ የደንበኛውን የሰውነት ሙቀት ሲለካ።
የምስሉ መግለጫ, በሚላን ጣሊያን በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ አስተናጋጁ የደንበኛውን የሰውነት ሙቀት ሲለካ።
በሌባኖስ ቤይሩት በሚገኝ መስጅድ ውስጥ፤ ሙስሊሞች ጸሎት ሲያካሂዱ በዚህ መልኩ ርቀታቸውን በመጠበቅ ነው።
የምስሉ መግለጫ, በሌባኖስ ቤይሩት በሚገኝ መስጅድ ውስጥ፤ ሙስሊሞች ጸሎት ሲያካሂዱ በዚህ መልኩ ርቀታቸውን በመጠበቅ ነው። በመስገጃ ምንጣፉ ላይ የተቀረጸው ስዕል ሰዎች ርቀታቸውን በቀላሉ እንዲያውቁ ያስችላል።

የሁሉም ፎቶግራፎች የባለቤትነት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።