ኢራን
እና አሜሪካ ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ አገራት የሚመረተው ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እና ጋዝ ይተላለፍበት የነበረው የሆርሙዝ ወሽመጥ
በቁጥጥራቸው ሥር መሆኑን እየገለጹ ባለበት በአሁኑ ጊዜ የወሽመጡ መከፈት አጠያያቂ ሆኗል።
ኻታም
አል አንቢያ የሚባለው የኢራን የጦር ኃይሎች ማዘዣ ማዕከል ከፍተኛ አዛዦች መካከል አንዱ፣ “የሆርሙዝ ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ
በኢራን የጦር ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
በተመሳሳይም
የአሜሪካ ጦር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) በበኩሉ በኢራን ወደቦች ላይ የተጣለው የባሕር እንቅስቃሴ ዕገዳ ተግባራዊ
መሆኑን እንደቀጠለ ገልጾ፣ እስካሁን 130 የንግድ መርከቦች ላይ ክልከላ በመጣሉ ወደመጡበት መመለሳቸውን አስታውቋል።
ብርጋዲየር
ጄነራል ሻምኻል ጃፋሪ ለኢራን ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ደግሞ “የጠላት መርከቦች እና የባሕር ላይ ወታደራዊ መሣሪያዎች ከኢራን እስላማዊት
ሪፐብሊክ ጠረፎች በጣም ርቀው እንዲሰማሩ አስገድደናቸዋል” ብለዋል።
እንዲሁም
የኢራን ኃይሎች ከተቃራኒው ወገን መሣሪያዎችን “ማርከዋል” በማለት ገልጸዋል፤ ነገር ግን ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጡም።
በሌላ
በኩል፣ ሴንትኮም በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፣ በኢራን ላይ የተጣለውን የባሕር ዕገዳ በማስፈጸም ሂደት 130ኛውን የንግድ መርከብ ወደ
መጣበት እንዲመለስ መደረጉን አስታውቋል።
እንደ
የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ መረጃ፣ በኢራን ላይ የተጣለው ዕገዳ በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትዕዛዝ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ እንደገና
የተጀመረ ሲሆን፣ ወደ ኢራን ወደቦች ለመግባት ወይም ከኢራን ወደቦች ለመውጣት የሚሞክሩ መርከቦች እንዳይንቀሳቀሱ የሚደያርግ ዕገዳ
ነው።
ዕዙ
በተጨማሪ የአሜሪካ ኃይሎች ትዕዛዛቸውን ያልተከተሉ ሦስት መርከቦችን እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ እርምጃ እንደተወሰደባቸው እና ባለፉት
ሦስት ወራት ውስጥ 13 የንግድ መርከቦችን ማውደማቸውን አስታውቋል።
ሴንትኮም
እነዚህ መርከቦች ዕገዳውን ጥሰዋል ወይም በኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይሎች የሚመራ በቢሊዮኖች ዶላር የሚገመት ሀብት የሚያንቀሳቅስ የምሥጢራዊ እንቅስቃሴ አካል ነበሩ ብሏል።
የአሜሪካ
ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ብራድ ኩፐር የአሜሪካ ጦር ኃይል በዚህ ተልዕኮ ላይ አተኩሮ እንደሚቀጥል እና ዕገዳውን ለማለፍ በሚሞክሩ
መርከቦች ላይ ፈጣን እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል።
ሴንትኮም
መርከበኞች በኦማን ባሕር እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ሲንቀሳቀሱ የባሕር ላይ መመሪያዎችን እንዲከተሉ እና በሬዲዮ ቻናል 16 በኩል
ከአሜሪካ ባሕር ኃይሎች ጋር እንዲገናኙ አሳስቧል። ሆኖም የአሜሪካ መርከቦች የት እንደሚገኙ ወይም ከኢራን ድንበር ምን ያህል
እንደራቁ አልገለጸም።
የኢራን
ወታደራዊ ባለሥልጣናት በቅርብ ቀናት ውስጥ የአሜሪካ መርከቦች ከአካባቢው እየራቁ እንደሆነ ደጋግመው ሲናገሩ ቆይተዋል።
የአብዮታዊው ዘብ ዋና አዛዥ አማካሪ ቦርድ ኃላፊ አድሚራል አሊ ፋዳቪ በቅርቡ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ፣ በሆርሙዝ ሰርጥ፣ በኦማን ባሕር
እና በሰሜናዊ ሕንድ ውቅያኖስ ላይ የአሜሪካ ወታደራዊ መርከብ እንደማይንቀሳቀስ እና የአሜሪካ ኃይሎች ከኢራን ድንበር
ከ1,000 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የኢራን
ጦር ኃይሎች ምክትል አስተባባሪ አድሚራል ሃቢቦላህ ሳያሪ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ወደ ደቡባዊ ሕንድ ውቅያኖስ ማፈግፈጓን እና
የባሕር ላይ ዕገዳውን ከኢራን የጦር መሣሪያዎች የርቀት ክልል ውጭ ሆና እያስፈጸመች መሆኑን ተናግረዋል።
ኢራን
የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ እንደምትቆጣጠር ማሳወቋን እንዲሁም ሴንትኮም የዘረዘራቸውን እርምጃዎች እና አሃዞች ከገለልተኛ
ምንጮች እስካሁን አልተረጋገጡም። እንዲሁም በኢራን ወደቦች ላይ የቀጠለው የባሕር ላይ ዕገዳ ብቻውን የሆርሙዝ ወሽመጥን በሙሉ
ቁጥጥሩ ሥር ማዋሉን አያረጋግጥም።